Tuesday, November 6, 2012

ዐቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን የG8 አባላት የሆኑት ሦስቱ የጉድ ሙዳዮች አላሠራ ስላሏቸው የሕግ ያለህ እያሉ መሆናቸው ተሰማ።


ምንጭ፡ አባ ሰላማ (Monday, November 5, 2012)

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የሾሟቸው ነገር ግን ተመልሰው ጠላት የሆኗቸውና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በማበር ልዩ ልዩ ሤራዎችን በመጠንሰስና በማሳደም እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ድረስ ሲያሳዝኗቸው የኖሩት የጉድ ሙዳዮች አባ ሳሙኤል፣ አባ አብርሃም እንዲሁም አባ ሉቃስ፣ ከዐቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ጋር መጋጨታቸው ተሰማ። የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ዜና ዕረፍት ተከትሎእንዳሻን እናደርጋቸዋለንበሚል የመረጧቸውንና ከሾሟቸው በኋላ» ግን ቋሚ ሲኖዶስ እያለ ዐቃቤ መንበሩን እንረዳለን በሚል ተመሳጥረው የተሰየሙትና 8 አባላት የሚገኙበትና «G8» እየተባሉ የሚጠሩት የጳጳሳት ቡድን፣ እንደፈለጉት ያልሆኑላቸውን አቡነ ናትናኤልን አላሰራ ብለው ሲያስቸግሯቸው እንደቆዩ የገለጹት ምንጮቻችን አሁን ነገሩ ጦዞ ወደአልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመራ ተሰግቷል ይላሉ።

የአቋም ሰው መሆናቸው የሚነገርላቸው አቡነ ናትናኤል የእነዚህንጳጳሳትአላሠራ ማለት ተከትሎ፥ «የፓትርያርኩ ሥልጣን ምንድነው? ሥራ አስኪያጁስ የሚሠራው ምንድነውበሚል ጠይቀው ከመጋቤ ስርአት አሰፋ ስዩም ደንቡ ቀርቦላቸው ስልጣናቸው በሚፈቅድላቸው መሰረት ሥራውን ላከናውን ቢሉም «ያለእኛ ፈቃድ አንድም ነገር ማድረግ አይችሉም» የሚል ማስጠንቀቂያ ከእነዚሁ ጳጳሳት ደርሷቸዋል። ይህም «እርስዎ አሻንጉሊት እንጂ ሥልጣኑ ያለው በእኛ እጅ ነው» የሚል አንደምታ እንዳለው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ያስረዳሉ። ይህን ተከትሎም አቃቤ መንበሩ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል «አንድም ነገር ማድረግ የማልችል ከሆነ ከዚህ በኋላ አልሰበስባችሁም፤ ለሚመለከተው የመንግስት አካል አቤት እላለሁ» በሚል ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አቤት ለማለት እየተዘጋጁ መሆናቸው ተሰምቷል። እንደሚታወቀው አቃቤ መንበር ፓትርያርክን ወክሎ የሚሰራ በመሆኑ ፓትርያርክ ተመርጦ መንበሩን እስኪይዝ ድረስ የፓትርያርኩን ተግባራት ያከናውናል። የቤተ ክርስቲያንን ሕግ ለራሳቸው በሚስማማቸው መንገድ እየለወጡ የሚፈልጉትን ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ያሉት «G8» የተባለው የጳጳሳት ቡድን ግን ራሳቸውን የአቃቤ መንበር ደጋፊ አድርገው በማቅረብ የጀመሩት ጉዞ ወደፍጹም ፈላጭ ቆራጭነት ተሸጋግሮ እነሆ አቃቤ መንበር ናትናኤልን አላሰራ ብሏቸዋል። ከመጀመሪያውኑ ቋሚ ሲኖዶስ እያለ የእርሱን ሥራ የሚተካ ቡድን መፈጠሩ በአንዳንድ ጳጳሳት ተቃውሞ የገጠመው ቢሆንም ማንም ሊያቆመው ግን አልቻለም። አሁንማ ለእነርሱ የሚመቹ አንቀጾችን በሚወጣው ሕግ ውስጥ እንዲካተት ለማድረግ እየሰሩ መሆናቸው ይሰማል፡፡ ጉዳዩ በዚሁ ከቀጠለ ቤተክርስቲያኗ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደምትገባ እየተነገረ ነው።

ከዚህ በፊት እውነተኛ ታሪካቸውን ይፋ እንዳደረግነው እነዚሁ አባ አብርሃም አባ ሳሙኤልና አባ ሉቃስ ለጵጵስና በሚገባ ቅድስና ውስጥ የሌሉና የጋብቻ ወግ በሌለውና ለመናገር በሚከብድ የቅድስና ችግር ውስጥ የሚገኙ ናቸው። አንዳንዶቹ እንዲያውም በግብረ ሰዶማዊነት ሲኖዶስ ላይ ተከሰው የቀረቡ ቢሆንም ጉዳዩ ተድበስብሶ መቅረቱን ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። የዘርአ ያእቆብ ገዳይ መንፈስ የሰፈረበት የማኅበረ ቅዱሳኑ ማንያዘዋል ሰሞኑን የሚያድረው አባ ሉቃስ ቤት ነው እየተባለ በአይን ምስክሮች ይፋ የሆነው መረጃ ደግሞ፣ አባ ሉቃስ ጳጳስ ከመሆናቸው በፊት ዲላ ላይ አንድ ሆቴል ውስጥ አንዱን ጎረምሳ አንቀው ይዘውት እንደነበረና ሲጮህ መልቀቃቸውንና እርሱም እግሬ አውጪኝ ብሎ ማምለጡን አስታውሰው ያን ታሪክ አሁን ከማንያዘዋል ጋር እየደገሙት ነው የሚል ወሬ ቤተክህነት አካባቢ በሰፊው እየተናፈሰ ነው።    

መቼስ «ጳጳስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ» ሆነና ነገሩ የሚጠይቅ አካል ጠፋ እንጂ፥ እንዲህ ባለው የስነምግባር ችግር ውስጥ እያሉ እንኳን ለሚመኙት ፕትርክና ይቅርና ከጵጵስናውም የሚሻሩ ነበሩ። ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ እነርሱ ከሕግ በላይ ስለሆኑ እንዲህ እየሆኑም ተከብረው ይኖራሉ። በአሁኑ ወቅት ከሲኖዶስ ስብሰባ ጋር ተያይዞ ቤተ ክርስቲያኗን እናሽከረክራለን የሚሉት እነዚሁ የጉድ ሙዳዮች መሆናቸው ሲታይ ደግሞ እግዚአብሄር ይህችን ቤተክርስቲያን እየተዋት ለመሆኑ ትልቅ ማሳያ ነው የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም። ለእነዚህ የጉድ ሙዳዮች ባህሪያቸውን የሚገልጽ ስም እዚያው ቤተክህነት ውስጥ የወጣላቸው ሲሆን የሚጠሩትም

አብርሃም መሰሪ
ሳሙኤል አጭበርባሪ
ሉቃስ አታላይ
ሕዝቅኤል አስመሳይ እየተባሉ ነው።

No comments:

Post a Comment