Wednesday, May 9, 2012

አባትነት በገንዘብና በፖለቲካ ሲፈተን

ከታዛቢ

ብፁዕ አቡነ አብርሃም  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከምአመናን ተለምኖ በተገኘ ገንዘብ የተገዛውን የዲ.. እና አካባቢው መንበረ ጵጵስና /ቤት እንዲያስረክቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወሰነ።

ማኅበረ ቅዱሳን እያለ ራሱን በሚጠራው ድርጅት አቀንቃኝነታቸው  የሚታወቁት  ወጣቱ ጳጳስ አቡነ አብርሃም በአሜሪካ በተለያየ ስቴቶች በተካሄዱ ጉባዔያት አማካይነት ከምእመናን በተሰበሰበ የአሜሪካ ዶላር 265 000.00 የተገዛው መንበረ ጵጵስና በራሳቸው እና በወሮ. ሀረገወይን ስም ለምን ለማዛወር እንደፈለጉ ባይታወቅም መንበረ ጵጵስናው የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ንብረት መሆኑ እየታወቀ አላስረክብም  ማለታቸው በዘመናዊ አነጋገርየመርካቶ ቁጩ  ዐይነት ቢሆንም የኢትዮጵያና የአሜሪካ መንግሥታት እንዲያውቁት  ተደርጎ በአስቸኩዋይ እንዲያስረክቡ ከዚህ በታች አባሪ በሆነው ደብዳቤ መታዘዛቸውን ቤተ ክርስቲያን ገለጸች።

መቼም መስከራም  ሳይጠባእንደሚባለው የዋሽንግተንና አካባቢዋ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል መንበረ ጵጵስናውን በሥርዐት እንዲያስረክቡ በተደጋጋሚ ቢጽፍላቸውም አሻፈረኝ ብለው መንበረ ጵጵስናውን ለማኅበረ ቅዱሳን /ቤት (ደጀ ሰላምና አሃቲ ተዋህዶ ብሎግ ማዘጋጃ) አከራይተው  እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ  ታውቁዋል። አኒህ ጳጳስ እንደሚታወቀው ቀደም ሲል ከመርካቶው  ራጉኤል ቤተ ክርሰቲያን ባካበቱት  (በዘረፉት ቢባልም ሥራቸው ነውና ራሳቸው ይፈሩ!) ገንዘብ .ኤም.. አጠገብ ፎቅ ቤታቸውን ሠርተው ሳያፍሩ ያስመረቁ ሲሆን፣ በቅርቡም በባንክ ሂሣብ የተጠራቀመውን ከዲ. ከወሰዱት  የሀገረ ስብከቱ ገንዘብ እና አቶ አሥራት ከሚባል (የጎጃሙ ባለአውሊ) የተቸራቸውን ብር 400 000.00 በመጨመር  ሁለት ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ገንዘብ ልዩ  ላንድ ክሩዘር ገዝተው -መንፈሳዊ የሆኑ  ተግባራትን ያከናውኑበታል።

ያዳቆነ ሠይጣን ሳያቀስ አይለቅምእንደሚባለው አዋሳ ትኩረታቸውን በማድረግ ለመዛወር የድጋፍ ድምጽ እያሰባሰቡ ነው ይባላል።  የአዋሳ ሕዝበ ክርስቲያን እምነቱን ለመዝባሪ አሳልፎ  እንደማይሰጥ በተደጋጋሚ ያረጋገጠ ነውና ሙከራቸው ፋይዳ እንደማይኖረው ተስፋ እናደርጋለን፣  በሌላ በኩል ማኅበረ ቅዱሳን በአዋሳ የፈጠረውን ችግርና መንግሥት እንዴት እንደፈታው እየታወቀ አባ አብርሃም በጥቅም ለቆሙለት ማኅበረ  ቅዱሳን አዋሳ ላይ ርስቱን ሊያስመልሱለት ቃል የገቡ ይመስላል፣ ግንሞኞ ሆይገደሉን ሳታይእንደሚባለው በዚህ አካሄዳቸው ከማን ጋር እንደሚላተሙ አዙረው ማሰብ አልቻሉም ማለት ነው - ገንዘብ ያውራል ይባል የለ !

ማኅበረ  ቅዱሳን በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያንን ተጠልሎ  ምእመናንን እየከፋፈለ የፖለቲካ መሣሪያ እስከማድረስ የሚያደርገው ተልእኮ እንዲቀጥል ለቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አቅርቤ አቡነ ፋኑኤልን አስነሳለሁ በማለት ገንዘብና ተወካይ ላኩልኝ ባሉት መሠረት ገንዘቡም መልእክተኞችም (ከአሜሪካ አባ ዘሊባኖስና አባ ገብረ ወልድ) መጥተው አባ አብርሃም ቤት በሰሞኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ጳጳሳትን ለመከፋፈል በዱለታ ላይ ይገኛሉ፣ ለተቀደሰ አገልሎት ሊውል የሚገባውን ገንዘብና ጊዜ ጳጳሳትን ለመደለል ሲያባክኑት ዲያብሎስን በመወከል የአድማ ምንጭ ሆነዋል። መቼም በቤተ ክርስቲያናችን የእምነትና ትምህርት ክህነት በገንዘብ አይሸጥም፣ ለአድማ ተግባርም አይውልም። አባ አብርሃም ግን የማኅበረ ቅዱሳንን የአድማ ተልዕኮ ለማጠናከርና የገንዘብ ምንጫቸው እንዳደርቅባቸው፡ -

1. ዶር. መስፍን የሚባለውን ምእመን ለቴነሲ ኪዳነ ምህረት አለቃ፣
2. ብርሃኑ ጎበና ለሜሪላንድና ፔንሲልቫንያ ኪዳነ ምህረት አለቃ፣
3. ቀሲስ ያሬድ /መድኅን ለኦሃዮ ገብርኤል አለቃ፣
4. አቶ በላቸው ወርቁ (ፓርላማ የነበረና ጥገኝነት ጠይቆ የሚኖር) ለኒዮርክ ኪዳነ ምህረት አለቃ፣
5. አቶ ገብረ ወልድ (ድሮ አባ የነበሩ ግን ከተለያዩ ሴቶች ልጆች ያፈሩ) ዳላስ አጠገብ ለሚገኘው ለቨርጂኒያ ራጉኤል አለቃ አድርገው በመሾም ከአባቶች አንዱ ነኝ የሚሉዋትን ቤተ ክርስቲያናቸውን አዋርደዋል፣  ሀረገ ስብከቱንም የፖለቲካ  መናቆሪያ አድርገዋል። ይኽ እንግዲህ መንግሥት ለረጅም ጊዜ በትእግስት ይዞት የነበረውን የሰለፊያንን ጉዳይ በሳቸው ሀገረ ስብከት እንዲጠናከር ሲያደርጉ የት ላይ ለመቆም ፈልገው እንደሆነ ከወዲሁ ሊታይና ሃይ ሊባሉ ይገባል።

እንግዲህ አባ አብርሃም ዋሽንግተን በቆዩበት ጊዜ የግል ሥራቸውን ሲያሳድዱ መደበኛ ሥራቸው የተጎዳ መሆኑ፣ አብያተ ክርስቲንን ለመከፋፈል ሙያው የሌላቸውን የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ሥልጣነ ክህነት እየሰጡ በመሾም ትርምሱን ለማጠናከር እንደሞከሩ ከአሠሪያቸው /ቤት በተጻፈላቸው ደብዳቤ ላይ ተጠቅሱዋል።  ይች ቤተ ክርስቲያን እንደአባ አብርሃም ያሉ አባቶች የሚመሩዋት ከሆነ ከሀገርም አደጋ  ነውና ቅዱስ ሲኖዶስም ምእመናንም ሊታገሉዋቸው ይገባል።

እግዚአብሔር ለአባ አብርሃም ልብ እንዲሰጣቸው፣ ጤናቸውንም እንዲመልስላቸው እንጸልይላቸዋለን

በሀዋሳ አሥር የማይሞሉ ጥገኛ ነጋዴዎች አቡነ ገብርኤል ከቦታቸው እንዳይነሱ የድጋፍ ድምጽ በማሰባሰብ ላይ ናቸው ተባለ


የየአጥቢያ አስተዳዳሪዎችም ማመልከቻዎቻቸውን ፋክስ እንዲያደርጉ ተገደዋል ተብሏል

በሀዋሳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናንና የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር መካከል ለሁለት ዓመታት ያህል የዘለቀ ግጭት ሰፍኖ መቆየቱ ይታወሳል፡፡  በዚህም ግጭት አቡነ ገብርኤል ማኅበረ ቅዱሳንን ከላይ እስከ ታች ባሉ የቤተክርስቲያኗ አስተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ ሰግስገው ያስገቡ ሲሆን፣ ባሳዩት የመልካም አስተዳደር ግድፈት በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናንና ምዕመናት ከቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ተባርረውና ተሰደው የሚገኙ መሆናቸውን የተለያዩ ብሎጎችና የዜና ምንጮች መዘገባቸው አይዘነጋም፡፡

አቡነ ገብርኤል በሀዋሳ ግጭት አፈታት ከቅዱስ ሲኖዶስ ልዩ ጽ/ቤት እና ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በተለያዩ ጊዜያት የወጡ መመሪያዎችን፣ ትዕዛዛትንና ማሳሰቢያዎችን በመጣስ ግጭትን የሚያባብሱ እርምጃዎችን ሲወስዱ መቆየታቸውና ለሠላም የሚደረገውን ጥረት ሆን ብለው ሲያደናቅፉ እንዲሁም የዐዋቂ አጥፊ ሆነው ከዳንስ ቤቶች ባለቤቶችና አሥር ከማይሞሉ ጥገኛ ነጋዴዎች ጋር በማበር ንጹሐን ምዕመናንን ሲያስደበድቡና ሲያሳስሩ መክረማቸው በገሃድ የሚታወቅ ነው፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ከአንድም ሦስት ጊዜ (ማለትም ግንቦት 2003 ዓ.ም፣ ጥቅምት 2004 ዓ.ም እንዲሁም ታኅሣሥ 2004) መደበኛና ልዩ አስቸኳይ ጉባዔ ጠርቶ በአቡነ ገብርኤልና በሀዋሳ ምዕመናን መካከል የቆየውን ግጭት ለመፍታት አጀንዳ ቢይዝም፣ አቡነ ገብርኤል ሆን ብለው ከጉባዔው መካከል ባለመገኘትና ግብረ አበሮቻቸው ደግሞ እርሳቸው በሌሉበት የእርሳቸውን ጉዳይ አናይም በማለት የምዕመናን ዕንባና ደም የትም ፈሶ እንዲቀር ፈርደውበታል፡፡

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በማኅበረ ቅዱሳን በኩል ተልዕኳቸውን የጨረሱ መሆናቸው ታውቆ አቡነ አብርሃምን በእርሳቸው ቦታ ላይ ለመተካት ጥረት በመደረግ ላይ ሲሆን፣ ጥገኛ ነጋዴዎቹ ደግሞ በበኩላቸው እርሳቸው ከሄዱብን ኦዲት የሚያደርገን ሊቀጳጳስ መጥቶ ጉዳችን ይወጣል፤ እንዋረዳለን ከሚል ስጋት በትላንትናው ዕለት ምሽት (ማክሰኞ ሚያዝያ 30 ቀን 2004 ዓ.ም) እርሳቸው እንዳይነሱባቸው በከተማዋ አጥቢያ ቤተክርስቲያናትና ልዩ ልዩ ሥፍራዎች በመሯራጥ የድጋፍ ድምፅ ለማሰባሰብ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ (በነገራችን ላይ ጥገኛ ነጋዴዎቹ ከዚህ በፊት ምንም ያልነበራቸውና ከሀዋሳ ከቅዱስ ገብርኤል ገዳም በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በመመዝበር ራሳቸውን ያደራጁ መሆኑ በብዙዎች ዘንድ ይታመናል፡፡ ከዚህም በላይ እነዚህ ጥገኛ ነጋዴዎች ቅን የቤተክርስቲያን አገልጋይ በመምሰል፣ ሰባት ያህል አጥቢያ ቤተክርስቲያናት በሰበካ ጉባዔ አባልነት፣ በልማት ኮሚቴና በበጎ አድራጎት ስም ተሰግስገው እዚህም፣ እዚያም ያለ አጥቢያቸው በመወራጨት የቤተክርስቲያኗን የመልካም አስተዳደር ገጽታ ያበላሹ መሆኑ በይፋ ይነገራል)፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም የየአጥቢያ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎችም አቡነ ገብርኤል ከቦታቸው እንዳይነሱ ማመልከቻዎቻቸውን ፋክስ እንዲያደርጉ በእጅ አዙር የተገደዱ ሲሆን፣ አሥር ከማይሞሉት ጥቂት ነጋዴዎች መካከል ብርሃን እና አዳነ የተባሉ ግለሰቦች እዚህም እዚያም ተሯሩጠው የሸከሸኩትን ፊርማ አሰባስበው ሌሊቱን በመጓዝ ከጥሩ የእጅ መንሻ ጋር ጠቅላይ ቤተክህነት አባቶች ዘንድ ከተፍ ብሎ "የሀገር ያለህ"!! ብለው እንደለመዱት በሐሰት ለመጮኽና መሬት ላይ ለመንከባለል ዕቅድ መያዙ ተረጋግጧል፡፡ ይሁን እንጂ ለእነዚህ ጥገኛ ነጋዴዎችና ማኅበረ ቅዱሳን ምቾት ካልሆነ በስተቀር አቡነ ገብርኤል ማናቸውም ፀጉር የሚያስነጭ መንፈሳዊ ፍቅር፣ አገልግሎትና አርአያነት ያለው መንፈሳዊ ፍሬ የሌላቸው ናቸው (አራት ነጥብ)

በሰሞኑ የግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ሦስት ውጤት ይጠበቃል፡፡ እነዚህም፣
  1. አቡነ ገብርኤል በቦታቸው እንዲቆዩ ተደርጎ በያዙት የጥፋት ጎዳና የቤተክርስቲያን ሀብት እንዲመዘበር፣ ማኅበረ ቅዱሳን ራሱ ሃይማኖት ሆኖ እርሱ ያልፈቀደው ምንም ነገር እንዳይከናወን የፈላጭ ቆራጭ እና ሙስና የተንሰራፋበት ሥርዓት እንዲሰፍንና የተሰደዱት በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናንና ምዕመናት እንደወጡ እንዲቀሩ መፍቀድ፣
  2. አቡነ ገብርኤል ለይስሙላ ከቦታቸው ተነስተው፣ እርሳቸው የዘረጉት በማኅበረ ቅዱሳን የደነበሸ አስተዳደራዊ መዋቅር ባለበት ቆይቶ እንደ አቡነ አብርሃምና አቡነ ሳሙኤል ያሉትን ቀንደኛ የማኅበረ ቅዱሳን አራማጆችን በቦታው በመተካት የአሥር ሺዎች ምዕመናንን ሰቆቃ ማብዛት በየወገኑ እንደፍላጎቱ እንዲበተን አድርጎ ከእናት ቤተክርስቲያኑ ጋር ያለውን ቁርኝት እስከመጨረሻው መበጠስ፣
  3. አቡነ ገብርኤል ከቦታቸው ተነስተው፣ ከማኅበረ ቅዱሳን ንክኪ ነፃ የሆነ ቅን እና በሳል መንፈሳዊ አባት መድቦ፣ የቤተክርስቲያንን አስተዳደራዊ መዋቅር ከማኅበረ ቅዱሳን ንክኪ በማፅዳት፣ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩት ስደተኛ ምዕመናንና ምዕመናት ወደ እናት ቤተክርስቲያናቸው ተመልሰው ሠላም የሰፈነበት የአምልኮ ሥርዓት መመሥረት፣ ናቸው፡፡

እግዚአብሔር መንፈሱን በቅዱስ ሲኖዶስ ላይ አፍስሶ የሀዋሳ ምዕመናንና ምዕመናት ዕንባና ሰቆቃ ያበቃ ዘንድ በአቡነ ገብርኤል ምትክ በሳል፣ ቅንና መንፈሳዊ አባት መድቦ፣ የቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር ከማኅበረ ቅዱሳንና ከጥገኛ ነጋዴ ፀድቶ፣ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ የሀዋሳ ምዕመናን ወደ እናት ቤተክርስቲያናቸው ተመልሰው፣ ሁላቸውም ሠላም የሰፈነበት ሥርዓተ አምልኮ ይፈጽሙ ዘንድ ለዚያ ያብቃቸው እንላለን፡፡

የአብ ፀጋ፣ የወልድ ቸርነት፣ የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
የፃድቃንና ሰማዕታት ረድኤታቸው፣ የመላዕክት ጥበቃና ምልጃቸው፣
የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነቷ ከእኛ አይለይ!!!
አሜን!!!