Thursday, November 15, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን “ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ” የተባለ የንግድ ተቋም መመሥረቱ ተሰማ


ምንጭ:- Abaselama ብሎግ
Friday, November 9, 2012

በቤተክርስቲያን ስም ሃይማኖትን ሽፋን አድርጎ ፖለቲካዊ አላማውን ለማሳካት ላለፉት 20 ዓመታት  ሲንቀሳቀስ የቆየው ማኅበረ ቅዱሳን አሁን ካለው በበለጠ ኢኮኖሚያዊ ክንዱን ለማፈርጠምና በገንዘብ ሀይል ያሻውን ለማድረግ በማሰብ በቤተክርስቲያን ጥላ ስር ሆኖ ልዩ ልዩ የንግድ ተቋሞችን ከፍቶ ቀረጥ ሳይከፍል ከሌሎች ቀረጥ ከፋይ ነጋዴዎች ጋር እየተወዳደረ የቆየ ሲሆን፣ የንግድ ሜዳውን ይበልጥ ለማስፋት «ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ .» መመስረቱ ተገለጸ። ይህ የተገለጸው ማኅበሩ ለኅዳር 1/2005 በቸርችል ሆቴል ባዘጋጀው መርሀግብር ላይ አክስዮን የሚገዙ ሰዎች እንዲገኙለት በበተነው የግብዣ ደብዳቤ ላይ ነው።

ደብዳቤው የማኅበረ ቅዱሳን እንደሆነ የገለጹልን ግብዣው የደረሳቸው ምንጮች የማኅበሩ እንዳልሆነ ተደርጎ እየተዋወቀ ያለበት ሁኔታ መኖሩን ተናግረዋል። አክስዮን ማህበሩ በዋናነት በትምህርት ዘርፍ የሚሰማራ የንግድ ተቋም ሲሆን ስሙ እንደሚጠቁመው በኮንስትራክሽንና በኢንዱስትሪ ዘርፍም የመሰማራት እቅድ እንዳለው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሁለንተናው ማኅበረ ቅዱሳን ማህበረ ቅዱሳን እየሸተተ ለተቋሙ ምስረታ መነሻ የሆነው የማህበሩ የንግድ ተቋም የሆነው አቡነ ጎርጎርዮስ /ቤት መሆኑን ይገልጻል። «የማህበረ ቅዱሳን ንብረት አይደለም» ለማለት የሚሞክረው ደብዳቤው፣ «የዚህን /ቤት (የአቡነ ጎርጎርዮስን /ቤት) ዓላማ(ማለትም በእውቀት የበለጸገ፣ በስነምግባር የታነጸ፣ በኢትዮጵያዊ ማንነቱና መልካም ባህሉ የሚኮራ ትውልድ ማፍራት) የበለጠ ለማጠናከር ታስቦ የተመሰረተ ማኅበር ነው፡፡» በማለቱ ግን አምልጦት የማቅ ንብረት መሆኑን ራሱ በራሱ መስክሯል።

በማንኛውም ሁኔታ ሃይማኖትን ሽፋን ካላደረገ የሚሰማ የማይመስለው ማኅበሩ ገቢውን ለማሳደግ የመሰረተውን የንግድ ተቋሙን ዘርፍ «የተቀደሰ የስራ ዘርፍ» ማለቱ ግርምትን ፈጥሯል። በገዳማት፣ በአብነት ትምህርት ቤቶችና በገጠር አብያተ ክርስቲያናት ስም፣ በቅርቡም በዋልድባ ገዳም ስም የሚሰበስበውን ዳጎስ ያለ ገንዘብ ያለተቆጣጣሪ እንዳሻው ቤተክርስቲያን ውስጥ ለሚፈጽመው የሽብር ተግባር እያዋለው እንዳለ ይታወቃል፡፡ ከተሳካለት ከዚህ የንግድ ዘርፍ የሚገኘው ገንዘብም ለተመሳሳይ ተግባር የሚውል ነው። ከዚህ አንጻር እንዲህ ያለ የአመጻ ንግዱንና ቅድስናን ምን እንዳገናኛቸው ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም።

አክስዮን ማኅበሩ የማኅበረ ቅዱሳን አይደለም ማለት ለምን  እንዳስፈለገና አላማው ደግሞ የማቅን /ቤት በበለጠ ማጠናከር ነው መባሉ እርስ በርሱ የሚጣላ ነው። ማቅ ከዚህ ቀደምም ባንክ ለማቋቋም እንቅስቃሴ ጀምሮ የነበረ መሆኑን ዳንኤል ክብረት ማጋለጡ የሚታወስ ሲሆን የባንኩ ጉዳይ አሁን በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አልታወቀም። ለማንኛውም ማቅ ኢኮኖሚያዊ ጡንቻውን በማፈርጠም ቤተ ክህነቱንና ቤተ መንግስቱን ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ጉዞ ቀጥሏል።

No comments:

Post a Comment