Wednesday, February 29, 2012

"መረዋ" የምትባል አዲስ ብሎግ ተከፈተች!!

ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የሆናችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ሆይ!


እነሆ ስለቤተክርስቲያን እንቅስቃሴ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማቅረብ ይህችን ብሎግ ከፍተንላችኋል፡፡ ዓላማችን ተደጋጋሚ የሆነውን አንዳንድ የሐሰት መረጃን ከእውነት ጋር አገናዝቦ ለአማንያን ማቅረብ ነው፡፡


እንዳመቺነቱ ዜናዎችንና መንፈሳዊ ይዘት ያላቸውን ትምህርቶች እናቀርብላችኃለን፡፡ ቅንና ገንቢ አስተያየቶችን ስትሰጡን እንታነጻለን፡፡ ስለዚህ ይህንን እንድታደርጉ በእግዚአብሔር ስም እንማጸናለን፡፡ 

ሁላችንንም እግዚአብሔር ይርዳን!!!