ቅን አገልጋዮች ሲሰብኩ የረገሟቸውን እንደመረቁ አድርገው፣ የመረቋቸውን
እንደረገሟቸው አድርገው፣ በተለያየ ርቀት ያሉ ሰዎችን በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ እንደተቀመጡ አድርገው ፊልሙን ያቀነባበሩ እና ፊልሙን
ተመልክተው ያመኑ፣ አምነውም ለሌሎች አሠራጭተው ያሳሳቱ ሸረኞች ማቀርቀር ያለባቸው ጊዜ ቢኖር አሁን ነው፡፡ ምክንያቱም ቅን አገልጋይ
እህቶችንና ወንድሞችን ያለሥራቸው ኮንነዋል፣ ከስሰዋል፣ በድለዋል፡፡
ዘመድኩን ስለሠራው ወንጀል ዘብጥያ ወርዷል፡፡ ግን ዘመድኩንን
ሰማዕትና የሃይማኖት አርበኛ በማስመሰል "አርማጌዶን"ን ሲያውሱ፣ ሲሰጡ፣ ሲሸልሙና ሌላውን ሲያንቋሽሹ የከረሙትስ
ከኃጢአትና ከወንጀል ነፃ ናቸውን? የእነርሱስ አይብስምን? ንጹሐንን በሐሰት መክሰስ፣ የዋሃንን ከዕምነታቸው ማሰናክል ይቅር የሚባል
በደል ነውን?
ቢያንስ የኤማሁስ ሰዎች ለጌታችን፣ ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
እንደመሰከሩለት (ሉቃስ 24፤19)፣ "እነዚህ አገልጋዮች በዓይናችን እያየን የፈጸሙብን ነገር የለም" ብለን መመስከር
አቅቶን፣ እንደ "አርማጌዶኑ" ዘመድኩን "ተሃድሶ"!፣ "መናፍቅ!" እያልን ተንጫጫን፤ ባላየነው ባልሰማነው ግን፣ ዘመድኩን
ስለነገረን ብቻ፡፡
ዘመድኩን በቀለ የሊቃውንት ጉባዔንና የቅዱስ ሲኖዶስን ሥልጣን
በመጋፋት አገልጋዮችን "ተሃድሶ"!፣ "መናፍቅ!"
በማለት እየተሳደበ ቢዝነስ ሲሠራ፣ ሕግ ተላልፎ የሰውን ስም በማጥፋት ወንጀል ሲፈጽም፣ አንድ ክርስቲያን እንኳን "ተው
አንተ! እረፍ"!!
ያለው ሰው አልነበረም፡፡
ዘመድኩን ፊልሙን ለብቻው አልሠራዉም፡፡ ምርጥ የማኅበረ ቅዱሳን
ዕቃ እና የቆርጦ ቀጥሎች ተስፋ ነበር፡፡ ግና ምን ያደርጋል፣ ጉራውና ትዕቢቱ፣ መወጣጠሩ ዘብጥያ አወረደው እንጂ መንግሥተ ሰማያት
አላስገባውም፣ ወንድሙን ጨርቃም ብሎ የሚሳደብ ፍርድ እንደሚያገኘው ማን በነገረው?
ለማንኛውም፣ "አርማጌዶን" ቪ ሲ ዲን ያዘጋጀ፣
ያተመ፣ ያሠራጨ፣ የገዛ፣ የሸጠ፣ አይቶም "ትክክል ነው ብሎ" ሌሎችን ያሳሳተ ሁሉም ውሸታሞች ናቸው፡፡
አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ!!!
አንተ ብቻ ቅንና ትክክለኛ ፈራጅ ነህ፡፡
ከክፉ ጠብቀን፣ አድነንም!!!
አሜን!!!
No comments:
Post a Comment