Saturday, December 1, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ «ብላክ ማርኬት» እንዳለው ተሰማ


ምንጭ:- abaselama.eotc@gmail.com
Thursday, November 29, 2012

ድብቅ አላማ ይዞ በሃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሰው ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ቢሮ በድብቅ መክፈቱን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ እንደ ምንጮቻችን ከሆነ ማኅበሩ ለዚህ ህገወጥ ተግባር የሚጠቀምበት ቢሮ በስም «የቲዎሎጂ ምሩቃን ማኅበር» እየተባለ የሚጠራውና የቲዎሎጂ ምሩቃን በአባልነት የሌሉበትና ማንያዘዋልን ጨምሮ ጥቂት የማቅ «የቲዎሎጂ ምሩቃን» አባላት የሚገናኙበት ቢሮ ነው ብለዋል፡፡ ቢሮው ቀድሞ ከነበረበት ከቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ቢሮ እንዲያገኝ አድርጓል፡፡ ይህን ያደረገውም የውጭ ምንዛሬውን ጨምሮ ሌሎች ድብቅ ስራዎችን ለመስራትና ለመጠቀም አስቦ እንደሆነ ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ ቢሮው የማቅ ሌላው ቢሮ ነው እያሉም ነው፡፡ ማኅበሩ የዶላር ዩሮና ፓውንድ ምንዛሬዎችን የሚያካሂደው በድብቅ ሲሆን ከውጪ አገር ዶላር ይዘው የሚመጡና ዶላር የተላከላቸው የማኅበሩ አባላትና አንዳንድ ጳጳሳትም ዶላር ዩሮና ፓውንድ በዚሁ ቢሮ እንዲመነዝሩ እንደሚደረግ የደረሰን መረጃ ያመለከታል፡፡ መንግስት የዶላር እጥረት አጋጥሞኛል በሚልበት በዚህ ወቅት ማቅ እንዲህ እያደረገ መሆኑ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡
 
ማኅበሩ ይህን ህገወጥ ስራ እንዲሰራ የመደበው ሃይለ ማርያም አያሌው ዘላሊበላ የተባለውና በአሁኑ ጊዜ የምሩቃን ማኅበር ተብዬው ምክትል ሊቀመንበር መሆኑም ታውቋል፡፡ ምክትል ሊቀመንበር የሆነው ለሽፋን እንደሆነና ዋና ስራው ግን የማቅን የምንዛሬና ሌሎች ህገወጥ ስራዎችን ማከናወን እንደሆነ የሚናገሩት ምንጮች ግለሰቡ ከእጁ ትልቅ ቦርሳ እንደማይለይና እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ ለምንዛሬው ይዞ እንደሚንቀሳቀስ ተናግረዋል፡፡ ከአንዳንድ ከማህበሩ ጋር ንክኪ ካላቸው ኪራይ ሰብሳቢ የመንግስት ሰራተኞች ጋር በመመሳጠርም ኮንዶሚኒየም ቤት ላልተመዘገቡ የማህበሩ አባላት በህገወጥ መንገድ እንዲያገኙ ማድረግ የሃይለ ማርያም አያሌው ሌላው ስራ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮቻችን ኮንዶሚኒየም ያልተመዘገቡ አባላትን 20 ሺህ ብር በማስከፈል በፎርጅድ መረጃዎች ስማቸው ኮምፒውተር ላይ እንዲገባ የሚያደርግ ሲሆን ሲረከቡ ደግሞ 70 ሺህ ብር እንዲከፍሉ እንደሚያደርግ ምንጮቻችን ገልጸው እስካሁን 50 በላይ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን ለማኅበሩ አባላት ማሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ በዚህ ህገወጥ ስራ በሚሰበስበው ገንዘብ ለራሱ ጆሞ ሳይት ላይ 200 ሺህ ብር ባለሱቅ ኮንዶሚኒየም ቤት እና 30 ሺህ ብር 2 ጋሪ ከነፈረሶቹ ገዝቶ እያከራየ መሆኑንም ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆን ቤቱን ከማህበሩ እውቅና ውጪ ገንዘብ ወጪ አድርጎ በመግዛቱ ከማቅ ጋር ጭቅጭቅ ውስጥ ገብቶ እንደነበረና ካለረፋችሁ እኔም ሌላውን ሚስጢር እንዳላወጣ በማለት ስላስፈራራ ጉዳዩ ተከድኖ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ሃይለ ማርያም የላሊበላ ሰው በመሆኑና ባለጊዜዎቹንና የወንዙን ሰዎች እነአባ ህዝቅኤልን ስለተማመነ ቤተክህነት ውስጥ እንደልቡ እየተንቀሳቀሰ ነው ይላሉ፡፡ 

Thursday, November 22, 2012

ወደ ፍ/ቤት ሽማግሌ ይላካል አይላክም በሚል «አባ» ሳሙኤልና ጠበቆቻቸው ሳይስማሙ ቀሩ


ምንጭ:- አባ ሰላማ ብሎግ
Wednesday, November 21, 2012


የአባ ሚካኤል አስከሬን ወጥቶ እንዲመረመር ፍርድ ቤት ከወሰነ ወዲህ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገቡትና ነገሩን በሽማግሌ ለመጨረስ እየተንቀሳቀሱ ያሉት «አባ» ሳሙኤል ወደ /ቤት ይሄዱልኛል ያሏቸውን ሽማግሌዎች ያዘጋጁ ቢሆንም በጠበቆቻቸው በኩል ግን ሀሳቡ ተቀባይነት ሳያገኝና ሽማግሌም ሳይላክ መቅረቱ ተነግሯል፡፡ በጠበቆቹ በኩል የቀረበው ሐሳብ ተገቢነት ያለውና ህጋዊውን መንገድ የተከተለ  ሲሆን፣ «አባ» ሳሙኤልን «እርስዎ ጳጳስ ሆነው የሽምግልና ሕግን እንዴት አያውቁም? ሽምግልና እኮ እየተካሰሱ ባሉት ሁለት ወገኖች መካከል የሚከናወን የእርቅ ሂደት እንጂ ከፍርድ ቤት ጋር አይደለም፡፡ በፍ/ቤት ሕግ እንዲህ አይነት ሽምግልና ተሰምቶም ታይቶም አያውቅም» ብለዋቸዋል ተብሏል፡፡ አክለውም «ሽማግሌ መላክ ካለብንም መላክ የምንችለው የአባ ሚካኤል ልጅ ነኝ ወደሚለው ወደ ዮሐንስ ነው፡፡» ብለዋል፡፡

ይህን መቀበልና ከዮሐንስ ጋር ያላቸውን የክስ ሂደት በሽማግሌ መጨረስ ሽንፈትና ሞት መሆኑን የተረዱት «አባ» ሳሙኤል ግን ሐሳቡን መቀበል አልፈለጉም፡፡ ምክንያቱም ነገሩን በሽማግሌ መጨረስ የሚቻለው ዮሐንስ የአባ ሚካኤል ልጅ መሆኑን በመቀበል መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ለነገሩ በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደሞከርነው አባ ሚካኤል ልጃቸው መሆኑን ሳይክዱ እየረዱ እንዳሳደጉትና ለቁም ነገር እንዳበቁት «አባ» ሳሙኤልም ጭምር የታወቀ ነው፡፡ ይህ ነገር ይፋ መውጣቱ ግን ምእመናን ለጳጳሳት ያላቸው ክብር ግምት እንዲቀንስ የሚያደርግ በመሆኑ ከዮሐንስ ጋር ነገሩን በሽምግልና መጨረስ የማይታሰብ ነገር ነው፡፡ ውሳኔውን መቀበልም በሕግ ፊት የነገሩን እውነተኛነት ማረጋገጥ ነው፡፡ ከሁለቱ ክፉ ምርጫዎች የቱን እንደሚመርጡ የተቸገሩ የሚመስሉት «አባ» ሳሙኤል ሽማግሌ መላክ አለበት በሚለው አቋማቸው እንደጸኑ መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች እየተናገሩ ነው፡፡ ሳይማሩ የጠመጠሙት «አባ» ሳሙኤል ሽማግሌዎቹን እኔ አዘጋጅቻለሁ እናንተ የፍ/ቤቱን መንገድ ስለምታውቁት መንገዱን አሳዩኝ ብለው በአቋማቸው ቢጸኑም ጠበቆቹ የአባ ሳሙኤል ሀሳብ ከአንድ ጳጳስ የማይጠበቅና ያልተማረ ሰው እንኳን ያስበዋል ተብሎ የማይጠበቅ በመሆኑና /ቤትም በህግ የያዘውን ጉዳይ በህግ አግባብ ከመጨረስ በቀር የተጣላውና የተካሰሰው ወገን ስለማይኖር ሽምግልና የሚባል ነገር ስለማያስተናግድና ሀሳቡ ህጋዊ ባለመሆኑ ውድቅ በማድረግ ሳይተባበሯቸው ቀርተዋል፡፡


በዚህ የተበሳጩት «አባ» ሳሙኤል «እኔ እያመመኝ ነው፤ ዕረፍት ማድረግ አለብኝ» በሚል ወደ ኢየሩሳሌም መሄዳቸው ተሰምቷል፡፡ ምናልባትም በዚህ ሰበብ የፍርዱን የመጨረሻ ውሳኔ ላለማየት በሚል ይሁን ወይም በእርግጥ አሟቸው ለጊዜው የታወቀ ነገር ግን የለም፡፡